Back to Search
Start Over
Production, Preservation, and Utilization Patterns
- Source :
- Ethiopian Journal of Agricultural Sciences; Vol 28, No 3 (2018); 1-17
- Publication Year :
- 2018
- Publisher :
- Ethiopian Journal of Agricultural Sciences, 2018.
-
Abstract
- አህፅሮትይህ የመስክ ጥናት የተካሄደው በ2008 ዓ.ም. ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በተመረጡ የሰበታና በደሌ ከተሞች እንዲሁም ከአማራ ክልላዊ መንግስት በተመረጠ የደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ ነበር፡፡ የጥናቱ ዓላዎች በተመረጡት ከተሞች ውስጥ የሚገኙ የቢራ ፋብሪካዎችን ወቅታዊ የተረፈ-ምርት መኖ አቅም እንዲሁም በየከተሞቹ የሚገኙ ወተት ከብት አርቢዎችን የተረፈ-ምርት መኖዎቹን አከመቻቸትና አጠቃቀም ለማወቅ ነው፡፡ በዋነኛነት በሀገራችን የሚገኙ ፋብካዎች የቢራ ገብስ ጭማቂ መኖንና እርሾን የሚያመርቱ ሲሆን በ2008 ዓ.ም. ብቻ ከ12 የተለያዩ ፋብሪካዎች 26722.8 ቶን የቢራ ገብስ ጭማቂ መኖ (በድርቆሽ ይዘት) እና 360758.1 ሄክቶ ሊትር አርሾ ማምረት ተችሏል፡፡ የመኖ አመጋገብን በተመለከተ በከተሞች መካከል የነበረው የመሰረታዊ መኖ፣ ድጎማ መኖ፣ የቢራ ገብስ ጭማቂ ተረፈ-ምርት መኖ፣ ጨው እና አጠቃላይ ጥቅል ዕለታዊ የመኖ አመጋገብ ልዩነት በጣም የጎላ ነበር፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ በሰበታ የሚገኙ ታላቢ ላሞች የመኖ ፍጆታ ከበደሌ እና ደ/ብርሃን ከተማ ከሚገኙት ላሞች ፍጆታ የላቀ መሆኑን ለማስተዋል ተችሏል፡፡ የቢራ ገብስ ጭማቂ በወተት ከብቶች የወተት ምርት፣ ጥራትና እንስሳት ጤና ላይ የሚያስከትለውን ለውጥ ለማወቅ በአርቢዎቹ ላይ በተደረገ ጥናት የተገኘ ግብረ-መልስ እዳመለከተው ከወተት ጥራት በስተቀር በከተሞቹ መካከል ምንም የጎላ የግብረ-መልስ ልዩነት እደሌለ ለመረዳት ተችሏል፡፡የቢራ ገብስ ጭማቂን ሳይበላሽ ለረዥም ጊዜ ለማቆየት በሚያስችሉ ተለምዷዊ ዘዴዎችን ለመለየት በተደረገ ጥናት በጨው መዘፍዘፍ፣ በፀሐይ ሙቀት ማረድረቅና በገፈራ መልክ ማከማቸት እንደ ቅደም-ተከተላቸው ጥቅም ላይ የዋሉ መሆናቸውን ለመለየት ተችሏል፡፡ አቅርቦትን በተመለከተ በሰበታ ከተማ የሚገኙ አርቢዎች በተነፃፃሪነት የተሻለ የቢራ ገብስ ጭማቂ ተረፈ-ምርት መኖ አቅርቦት ሲኖራቸው የአንድ ኩንታል ደረቅ ተረፈ-ምርት መኖ ዋጋ በተጠኑት ከተሞች በአማካይ 82.50 እንደሚሸጥ ለማውቅ ተችሏል፡፡ የጥናቱ ከተሞች በዓመታዊ የጥቅል ገቢና ወጪ ክፍያዎቻቸው የሚለያዩ ሲሆኑ የሰበታ ከብት አርቢ በዓመት ለአንዲት ታላቢ ዲቃላ የወተት ከብት ከሚያወጣው ወጪ አንፃር ሲታይ በጥቅሉ በበደሌና ደ/ብርሃን ከተሞች ከሚገኙ አርቢዎች የላቀ ትርፍ በዓመት ማግኘት እንደሚችል ለመረዳት ተችሏል፡፡ Abstract The study was conducted at Sebeta and Bedele towns in Oromia regional state and at Debre-Berhan town in Amhara regional state during October-January 2016/17. The objectives of the study were; to assess the current feed byproduct production potentials of the breweries, existing storage conditions and the status of brewery spent grain utilization by smallholder dairy farms in the study areas. The result showed that brewery spent grain (BSG) and Brewer’s spent yeast (BSY) are the commonly produced byproduct feeds across all beer factories in Ethiopia. There were 12 beer factories producing an estimated 26722.8 tons BSG (DM basis) and 360,758.1 hectoliter (hl) of BSY in 2016 G.C... Substantial differences (P0.05). There was however, great variations in farmers’ response towards long term effect of BSG feeding on milk compositional changes (P
Details
- Language :
- English
- ISSN :
- 02572605 and 24152382
- Database :
- OpenAIRE
- Journal :
- Ethiopian Journal of Agricultural Sciences
- Accession number :
- edsair.78975075580c..06657b842154033f7720ea574f074c2c